የድጋፍ ሰነዶች ገጽ የቤተክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና ምዝገባ
የተከበራችሁ ምዕመናን
እንኳን ወደ ድህረገጻችን በሰላም መጣችሁ። በዚህ ገጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፖላንድ ሃገር ከተመሰረተች ረጅም ጊዜያት ቢቆጠሩም ሕጋዊ ምዝገባና እውቅና ስላላገኘች ይህንኑ እውቅና ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን መረጃ ያገኛሉ።
ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን ችላ አገልግሎት ለመስጠትና ከስርዓተ አምልኮዋ በተጨማሪ በሌሎች ሃገራት እንደምታደርገው ሃገራችንን፣ ታሪካችንንና ባህላችንን ለማስተዋወቅ በዚሁ ሃገር ልትመዘገብና ሕጋዊ እውቅና ሊኖራት ግድ ነው።
ይህንኑ ምዝገባና ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት በዋናነት የሚያስፈልገው ቢያንስ አንድ መቶ (100) የፖሊሽ ዜግነት ያላቸው ያላቸው እና እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፊርማ ነው። ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ በፖላንድ ሃገር በመቶች የሚቆጠሩ ምዕመናን ቢኖሯትም አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በመሆናቸው የፖላንድ ዜግነት የላቸውም።
እስካሁን ድረስ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ፊርማ ማግኘት የቻልን ቢሆንም ከዚህ በላይ ፊርማ ማግኘት ስላልቻልን የእናንተን ድጋፍ ልንጠይቅ ተገደናል። ፊርማውን ለመፈረም የግድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ መሆን አይጠበቅብዎትም። አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ይሄ ታላቅ፣ መንፈሳዊና ታሪካዊ አላማ እውን እንዲሆን የበኩልዎን ድርሻ በመወጣት ታላቅ አሻራዎን ያሳርፉ።
ስለ ሰነዱ አሞላል፣ አላላክ ወይንም ሌሎች ይሄን የተመለከቱ ጉዳዮች የሚከተሉትን ሰዎች ቢያናግሩ ፈጣን ምላሽ ይሰጡዎታል።
-
ወ/ሮ ሃዳስ [Hadas Trojanowska] (+48665347215) ---ul.inflancka 19/346, 00-189, Warsaw
-
ወ/ሮ አግኒሽካ [Agnieszka Garnyś] (+48609946996) --- ul.Wojska Polskiego 25/26, 70-470 Szczecin
(ከርሶ ሚጠበቅ ምንም አይነት ክፍያ የለም:: አስፈላጊ ወጪዎች በሙሉ በቤተክርስትያኑ ይሸፈናሉ::የእርሶን የፊርማ ትብብር ብቻ በእግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን)
ስለሚያደርጉልን ትብብር ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን!
ከሰላምታ ጋር!
የዋርሶ መንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን